Home » Barruulee » First Instance Court Commercial Bench Proceedings Code pdf
Mhaagj

First Instance Court Commercial Bench Proceedings Code pdf

የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንግድ ችሎቶች ሥርዓተ-ችሎት
1 / 6

መግቢያ

በአገር አቀፍ ደረጃ በፌዴራል ፍ/ቤቶች እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን ለማሻሻል በመከናወን ላይ ከሚገኙ ተግባራት እንዱ ችሎቶችን በጉዳያቸው አይነት በማደራጀት ጉዳዮችን በአፋጣኝ እና ጥራት ባለው መንገድ እልባት ለመስጠት የሚስችል አሰራር መዘርጋት ሲሆን ይህንኑ ለማሳካት በየደረጃው ባሉ ፍ/ቤቶች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ጨምሮ የንግድ ጉዳዮችን ብቻ የሚያስተናግዱ ችሎቶች እንዲቋቋሙ ተደርጓል። የንግድ ጉዳዮችን ብቻ የሚያስተናግዱ ልዩ ችሎቶች እንዲቋቋሙ ከማድረግ ባለፈ ችሎቶቹና የችሎቶቹ ዳኞች የሚመሩበትን ልዩ ሥርዓተ ችሎት ማዘጋጀት በዘርፉ የታለመውን ውጤት ለማምጣት እንደሚያስችል በኢትዮጵያ የፍርድ ቤቶች መዋቅር ከፍተኛው የስልጣን አካል በሆነው በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስተዳደር ታምኖበት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 16(1) ስር የተሰጠውን ስልጣን መሰረት በማድረግ ይህ ስርዓተ-ችሎት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እውቅና እና ፈቃድ ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንግድ ችሎቶች ሊዘጋጅ ችሏል።

ይህን የንግድ ችሎቶች ሥርዓተ-ችሎት (Commercial Proceedings Code) ማዘጋጀት ያስፈለገበት ዋና ዓላማ በችሎቶቹ የዕለት ተዕለት ተግባር ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ዳኞች በቀላሉና ሊፈቱ የሚችሉበትን መሪ ማጣቀሻ ለማዘጋጀት፤ ተከራካሪ ወገኖች እና የህግ ባለሙያዎችም በንግድ ችሎቶች የሚታዩ ጉዳዮችን እና ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ህግጋት በቀላሉ መለየት የሚችሉበትን ምቹ ሀኔታለመፍጠር፤ የንግድ ጉዳዮችን የተመለከቱ ክርክሮች መደበኛውን የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ተከትሎ ወጪ ቆጣቢ፤ ፈጣን እና ጥራት ባለው መንገድ በልዩ ሁኔታ የሚታዩበትን እድል ለማመቻቸት እንዲሁም በንግድ ችሎቶች ወጥነት ያለው የህግ አተረገጓጎም፤ የችሎት ሥነ ሥርዓት አተገባበር እና ቀጠሮ አሰጣጥ እንዲኖር ለማስቻል በማሰብ ነው።

ይህ ሥርዓተ-ችሎት አራት ዋና ዋና ክፍሎችን የያዘ ሆኖ የመጀመሪያው ክፍል በንግድችሎቶች የሚታዩ ጉዳዮችን ዓይነት በዝርዝር የያዘ ሲሆን በችሎቶቹ የሚታዩ ጉዳዮች ህጋዊ መሠረታቸው ምን እንደሆነ፤ የመብት ጥያቄዎቹ በማን እና በምን ሁኔታ ሊቀርቡ እንደሚገባ በአጭሩ ተብራርቷል። ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 በፍትሐ ብሔር ጉዳዮች የገንዘብ ግምታቸውን መሠረት በማድረግ የተሰጣቸው የዳኝነት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የንግድ ችሎቶች ከንግድ ተቋማት እና ከንግዱ ማህበረሰብ የእለት ተለት የንግድ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ በገንዘብ ሊተመኑ የማይችሉ ነገር ግን በውጤታቸው ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ አንድምታ ያላቸው ክርክሮች የሚታይባቸው ችሎቶች በመሆናቸው ይህን የችሎቶቹን ልዩ ባሕሪይ ታሳቢ በማድረግ የሚቀርቡ የመብት ጥያቄዎችን በዚሁ ክፍል ላይ ለመዳሰስ ተሞክሯል። visit or download👇 https://waagj.files.wordpress.com/2021/01/proc-no.-25-1996-federal-courts.pdf

የንግድ ጉዳዮችን የተመለከቱ ክርክሮች እንደማንኛውም ፍትሐብሔራዊ ጉዳይ ለጉዳዮች እልባት በመስጠት ሂደት የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጉን የሚተገብሩ ሲሆን የንግድ ችሎቶች ከባሕሪያቸው አኳያ ጉዳዮችን ለማየት የሚከተሉት ልዩ ስነ- ስርዓት በስርዓተ ችሎቱ ክፍል ሁለት ላይ በዝርዘር ተመልክቷል። ይህ የሥርዓተ-ችሎቱ ክፍል በአመዛኙ በፍ/ቤቶች ማሻሻያ ፕሮጀክት እና በፍትህ አካላት ስልጠና ማዕከል ትብብር በ1997 ዓ.ም ከተዘጋጀው “የፍትሐብሔር ክርክሮች ሥርዓተ ችሎት” ላይ የተወሰደ ሲሆን በንግድ ችሎቶች ከሚታዩ ጉዳዮች ልዩ ባህሪይ አኳያ የተጨመሩ ነጥቦችን እና በችሎቶቹ የጉዳዮችን ሂደት ለመቋጨት የሚያስፈልገውን የጊዜ ስታንዳርድ አካቷል።

የሥርዓተ ችሎቱ ሶስተኛ ክፍል በንግድ ችሎቶች የሚተገበሩ የቀጠሮ ፖሊሲዎችን የሚመለከት ሲሆን በቀጠሮ አሰጣጥ ረገድ የችሎቱ ዳኞች ምን የተለየ ስርዓት መከተል እንደሚገባቸው እንዲሁም የቀጠሮ ፖሊሲ አተገባበር ላይ የባለድርሻ አካላት ሚና እና ኃላፊነት ምን ሊሆን እንደሚገባው ተብራርቷል። ይህ ክፍል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል ካዘጋጀው ረቂቅ “የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍትሐብሔር እና መሠል ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ትግበራ መመሪያ” ላይ ለንግድ ችሎቶች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች በመውሰድ እና ሌሎች ከችሎቶቹ ልዩ ባህሪይ አኳያ በቀጠሮ አሰጣጥ ሂደት ሊተገበሩ የሚገባቸውን ነጥቦች በማካተት የተዘጋጀ ነው።

የስርዓተ-ችሎቱ መጨረሻ ክፍል የንግድ ጉዳዮችን የተመለከቱ ዋና ዋና ህግ ምንጮችን እና የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በንግድ ጉዳዮች ላይ የህግ ትርጉም የተሰጠባቸውን አብዬት ውሣኔዎች በአባሪ መልክ የያዘ ሲሆን የንግድ ጉዳዮችን የተመለከቱ ህግጋትን በቀላሉ ለማግኘት እንደሚያግዝ ይታመናል።

የዚህ ሥርዓተ-ችሎት ዋና መሠረቶች በዋነኝነት የንግድ ጉዳዮችን የሚመለከቱ መሠረታዊ ህጎች፤ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ፤ በንግድ ችሎቶች ለሚታዩ ጉዳዮች የተሰጠውን ልዩ ትኩረት ተከትሎ የተወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንዲሁም በችሎቶቹ የዳበሩ የአሰራር ተሞክሮዎች ሲሆኑ በንግድ ችሎቶች ከሚታዩ ጉዳዮች ልዩ ባሕሪይ አኳያ በመሰረታዊ ህጎቹም ሆነ በስነ-ስርዓት ህጉ አተገባበር ላይ ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዮችን በመጠኑ ለማብራራት ተሞክሯል። በሕጉ የተሸፈኑ ሆነው ነገር ግን በአተርጓጎምና በአተገባበር ረገድ ልዩነት የሚታይባቸውን የተወሰኑ ስነ-ስርዓታዊ ሂደቶችን በተመለከተ በተቻለ መጠን ልዩነቶቹ የሚጠቡበትን እና ሕጎቹ ወጥነት ባለው መልኩ የሚተገበሩበትን አቅጣጫ ለማሳየት ተሞክሯል

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *