Home » Barruulee » በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ደንብ ቀ

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ደንብ ቀ

የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር—

ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

መግቢያ

የወንጀል ሕግ አላማ ለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የአገሪቱን መንግስት፣ የህዝቦቹን፣ የነዋሪዎቹን፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ ስርአት፣ መብትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ነው፡፡

የወንጀል ሕጉ ከዚህ በላይ የተመለከተውን አላማ ለማሳካት ዋና ግቡም ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል ሲሆን፣ ይህንንም የሚያሳካው ለህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት አደጋ የሆኑ የወንጀል ተግባራትን እና እነዚህን መፈጸም የሚያስከትለውን ቅጣት ሰዎች አውቀው ከወዲሁ ከህገወጥ ተግባር እንዲቆጠቡ ማስተማርና ማሳወቅ ሲሆን፣ ይህ ሳይሳካ ቀርቶ ጥፋት አድራጊዎች ሲኖሩ እነዚህን ተገቢውን ቅጣታቸውን እንዲያገኙ በማድረግ ሌላ ወንጀል ከመፈጸም እንዲቆጠቡና ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈጽሙ እርምጃዎች እንዲወሰዱባቸው በማድረግ ነው፡፡

ቅጣት የወንጀል መከላከል ግቡን እንዲያሳካ ለእያንዳንዱ የወንጀል ድርጊት በወንጀል ህጉ መነሻና ጣሪያ የተቀመጠ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ በእነዚህ የቅጣት መነሻና ጣሪያ መሰረት ቅጣቱን ለመወሰን የሚያገለግሉ መርሆዎችንና መመሪያዎችን የያዙ ጠቅላላ የቅጣት አወሳሰን ድንጋጌዎችም በወንጀል ህጉ ተካተው ይገኛሉ፡፡

ይሁንና በወንጀል ህጉ ስለቅጣት አወሳሰን የተቀመጡት ድንጋጌዎች በፍርድ ቤት የሚሰጡ ቅጣቶች ወጥነት፣ ተመዛዛኝነት፣ ፍትሀዊ እንዲሆኑ ከማድረግ አንጻር ክፍተቶች እንዳላቸው  ግልጽ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ለተመሳሳይና ተቀራራቢ የወንጀል አፈጻጸሞች ተመሳሳይና ተቀራራቢ ቅጣት ለመጣል አስቸጋሪ እንደሚሆን መገመት ይቻላል፡፡

FSC sentencesing guidelines

Jimma zone attorney ofcie website

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *